አቶ አሰግድ ሙላት ከእናታቸው ወ/ሮ ሃረገወይን አስፋው እና ከአባታቸው አቶ ጋሼ ገብረ
መስቀል በታህሳስ 5 ቀን 1936 ዓ/ም በቀድሞ የወሎ ጠቅላይ ግዛት ወልድያ ከተማ
ተወለዱ።
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ትምህርት ቤት በመግባት
የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ። ሆኖም ግን በልጅነታቸው
እናታቸውን በሞት በማጣታቸው ምክኒያት አዲስ አበባ ወደሚኖሩት አጎታቸው አቶ
ሙላት ገብረ መስቀል ዘንድ በመሄድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአምሃ ደስታ
ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን፥ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወቅቱ ዝነኛ
በነበረው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አጠናቀዋል። ከዚያም አዲስ አበባ ንግድ ሥራ
ኮሌጅ (ኮሜርስ) በመግባት በማኔጅመንት ተመርቀዋል።
አቶ አሰግድ በልዩ ልዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በከፍተኛ
የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በእርሻ ምርምር: በቶማስ ቴለፍሰን በወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል - ኢትዮጵያና በሌሎችም መስሪያ ቤቶች ውስጥ በሃላፊነት አገልግለዋል።
አቶ አሰግድ በ1992 ዓ.ም ወደ አሜሪካ አገር እስከ መጡበት ጊዜ ድረስ በሙሉወንገል
ቤተክርስትያን በልዩ ልዩ አገልግሎት ክፍሎች ውስጥ ያገለግሉ ነበር።
አቶ አሰግድ የአራት ወንዶችና የአራት ሴቶች ልጆች አባት ሲሆኑ የዘጠኝ የልጅ ልጆች
አያት ነበሩ። አቶ አሰግድ ለ47 አመት የትዳር አጋራቸው ከሆኑት ከወ/ሮ ወይንሸት
ሃይለማርያም ጋር በፍቅር በመተሳሰብ ኖረዋል።
አቶ አሰግድ በሕይወት በነበሩበት ዘመን ለጋስ፤ አዛኝ፤ ቅንና ለሁሉም ሰው ተመሳሳይ
አመለካከት የነበራቸው፤ ከብዙ ወጣቶች ጋር በቅርበት የሚግባቡ ተራማጅ ሰው ሲሆኑ
ለልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው የኖሩ ደግ አባት ነበሩ።
አቶ አሰግድ ሙላት ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በተወለዱ በ75 አመታቸው
በድንገት ሕይወታቸው አልፏል። ለቤተሰባቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን
እንመኛለን።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
It is with great sadness that the family of Assegid Mulat announces his passing after a brief illness at the age of 75 on Saturday, March 9, 2019. Assegid will be lovingly remembered by his wife of 47 years, Woinshet, and his children, Menasseh (Tezita), Dorka (Solomon), Ermias (Deborah), Nefthalem, Meheret (Mezgebu), Wubet (Yonas), Nuhamin (Andy) and Solomon. Assegid will also be fondly remembered by his eleven grandchildren: Salem, Esther, Barkot, Blen, Noah, Nikolas, Makeda, Elelta, Dagim and two on the way. He will be also be remembered by his sister Wosenyelesh Teshome, and his brother Minale Gashe. Assegid was predeceased by his son Mulat Assegid and his sisters Tsehaynesh Teshome and Tsehaynesh Gashe.
A Funeral Service in memory of Assegid will be held on Friday, March 15, 2019 at 10:00 a.m at the Finley Sunset Hills Mortuary (6801 SW Sunset HWY Portland, OR 97225). Interment will follow in the family plot at Finely Sunset Hills Memorial Park at 12:00 PM. Luncheon to follow at Ammanuel Ethiopian Evangelical Church (3515 NE Killingsworth St. Portland, OR 97211). Those who so desire may make memorial donations in memory of Assegid to the family at 2503 NE Rodney Ave. Portland, OR 97212.
SHARE OBITUARY
v.1.9.5