

አብ ይካብ አየለ ከአባቱ ሜጀር ጀኔራል አለሙ አየለና ከእናቱ ከወይዘሮ ሐረግ ገብረ እግዚአብሔር በሰኔ 10 1994 ዓ/ም አዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። እስከ ሰወስተኛ ክፍል ድረስ አዲስ አበባ ከተማ የተማረ ሲሆን ቀሪውን የትምህርት እድሜውን ደግሞ አሜሪካ ውስጥ በኒውዮርክና ሜሪላንድ ተምሯል። 12ኛ ክፍልን ሮክቪል ከተማ በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በት አጠናቛል።
12ኛ ክፍልን እንዳጠናቀቀ የአሜሪካንን ሰራዊት በመቀላቀል በምድር ጦር ውስጥ በውጊያ መስመር በመካኒክነት ሞያ አገሩን አገልግሏል:: በአሜሪካ ሰራዊት ውስጥ በነበረው ቆይታ በስራ ታታሪነት:በወታደራዊ ዲስፕሊን እና በወታደራዊ የሞያ ችሎታውን በላቀ ብቃት በመፈፀሙ በተቛም ደረጃ በፕራይቬት ፈርስት ክላስና አውትስታንዲንግ አቺቭመንት ዊል አሳይንድ የተሰኙ ሜዳልያወችን ያገኘ ሲሆን እንዲሁም በቅርብ አለቆቹ ልዩ ልዩ ሽልማቶችንና አድናቆትን አግኝቷል። በአሜሪካ ሰራዊት ውስጥ የነበረውን አገልግሎት በክብር ተሰናብቷል: ከወታደራዊ አገልግሎት ከወጣ ቡሀላም በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፋየር ዲፓርትመን ውስጥ የበጎ አድራጎት አገልግሎት በመስጠቱ ተሸላሚ ሁኗል። ህይወቱ እስካለፈበት ድረስም ቤተሰቦቹ ጋር ሆኖ በሞንትጎመርይ ኮሌጅ በነርስንግ ሞያ ትምህርቱን ሲከታተል ነበር::
አብ ይካብ አለሙ አየለ በህይወት ዘመኑ ለማንም ሰው ትሁትና ታዛዥ:ለተቸገሩ ለጋሽ ያለውን የሚሰጥ:ለተገፉ ሁሉ ፍትህን ጠያቂና ሞጋች:ላመለበት እልኸኛና ቆራጥ:ሰውን ሁሉ አፍቃሪና የዋህ ልጅ ነበረ:: የቤተሰቡን ጥቃት የሚፀየፍ መካችና ቀድሞ ደራሽ ለወላጆቹ ታዛዥ የደግነትና የሰብአዊ ፍቅር ተምሳሌ ነበር። አሁን ልጃችን አብ ይካብ መልካም ምግባሩን ለግል ታሪኩ ትቶ አልፏል። እግዚአብሔር ሰጠን እግዚአብሔር ወሰደው ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። ነብሱን በደጋግ አባቶቻችን በአብርሃም በያይቆብ በይሳቅ እቅፍ ያስቀወጠው አሜን አሜን አሜን።
በዚህ የመከራ ጊዜ ከጎናችን ሳትለዩ በሀዘናችን አዝናቹህ እኛን ለማፅናናት በፆለታችሁ በጉልበታችሁ በገንዘባችሁ በምትችሉት ሁሉ ሳትሳሱ ያረጋችሁልንን ሁሉ እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈል። በዓለምና በደስታ ይመለስ። ከመሰል ሀዘንና መከራ ደጉ አምላክ እግዚአብሔር ይከልላችሁ። እናመሰግናለን! እናመሰግናለን! እናመሰግናለን!
Abycab Ayele — A Short Life History
Abycab Ayele was born to his father, Major General Alemu Ayele, and his mother, Mrs. Hareg Gebre Egziabher, on June 17, 2002, in Addis Ababa, Ethiopia. He attended school in Addis Ababa through third grade, then continued his education in the United States, studying in New York and Maryland. He completed 12th grade at Richard Montgomery High School in Rockville, Maryland.
After graduating from high school, Abycab joined the United States Army and served his country in the Army as a mechanic supporting the combat line. Throughout his service, he was recognized for his strong work ethic, military discipline, and professional excellence. He received honors, including advancement to Private First Class and an Outstanding Achievement award, along with additional commendations and recognition from his direct commanders. He completed his service with honor and was honorably discharged.
Following his military service, Abycab continued to serve his community. He was recognized for his volunteer service with the Montgomery County Fire Department. Until his passing, he lived with his family and was pursuing his education at Montgomery College, studying Nursing.
In his life, Abycab Alemu Ayele was known for his character. He was humble and respectful, generous to those in need, and a person who stood for justice and defended the vulnerable. He was determined and courageous, yet gentle and loving—someone who cared for others and treated everyone with kindness. He valued family peace, often acting as a peacemaker, and he was a devoted son—respectful, supportive, and quick to help his parents.
Abycab has left us, but he has left behind the legacy of his good character and the love he gave to others. As Scripture reminds us: “The Lord gave, and the Lord has taken away; blessed be the name of the Lord.” May God grant him eternal rest and place his soul in the bosom of the righteous—Abraham, Isaac, and Jacob. Amen.
During this time of grief, we are deeply grateful to everyone who has stood with us—sharing our sorrow, comforting us with your presence, and supporting us through your prayers, your help, and your generosity. May God reward you, return it to you in peace and joy, and protect you from such sorrow and hardship. Thank you. Thank you. Thank you.
COMPARTA UN OBITUARIOCOMPARTA
v.1.18.0