

“ጻድቅ ይሞታል፥ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፥ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም። ወደ ሰላም ይገባል፤ በቅንነት የሄደ በአልጋው ላይ ያርፋል።”
ኢሳይያስ 57:1
አቶ ሰለሞን አለማየሁ ከእናታቸው ከወ/ሮ ጽጌገነት ጨርቆስ አና ከአባታቸው ከፊትአውራሪ አለማየሁ ተፈራ ታህሳስ 26, 1957 በቀድሞ ሲዳሞ ክፍለሃገር በክብረ መንግስት ከተማ ተወለዱ::
እድሜያቸው ለትምህርት በደረስበት ወቅት አባታቸው ለፓርላማ አባልነት ስለተመረጡ ከቤተሰባቸው ጋር ወደ እዲስ አበባ በመምጣት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአስረ ሐዋሪያት በቅጽል ስሙ (አስፋው) ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመድኅኒያለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል :: አቶ ስለሞን ለእስፓርት ካላቸው ከፍተኛ ፍቅር የተነሳ በሚኖሩበት ቀበሌ በሚገኘው የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ በመግባት ባሳዩት ልዩ ብቃት ለቅዱስ ጊዎርጊስ ክለብ ተመርጠው ለጥቂት ጊዜ ተጫውተዋል:: እንዲሁም በኢትዮጵያ በነበሩበት ወቅት በወርልድ ቪዥን እለምእቀፍ ተቛም ውስጥ በመስራት አገራቸውን አገልግለዋል በተጨማሪም በኢትዮጵያ በሚገኘው በሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስትያን አባል ነበሩ ::
ወደ አሜሪካ እገር ከመጡ በኃላ የቴክኒክ ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን : በፖርትላንድ አማኑኤል ቤተክርስትያን በአባልነት ፣ በሸምግልና ፣ በመዘምራን ቡድን ውስጥ እና በፀሎት አገልግሎት ሲያገለግሉና ሲገለግሉ ቆይተዋል :: እንዲሁም በፓርትላንድ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ቡድንን በመቀላቀል ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ አስተዋጾ አድርጓል ::
አቶ ሰለሞን ከትዳር አጋራቸው ከወ/ሮ ዶርቃ አሰግድ ጋር በትዳር በቆዩበት የተባረኩ 18 አመታት በደስታና በመተሳሰብ የኖሩ ሲሆን:: በትዳራቸውም ሁለት ሴት ልጆችና አንድ ወንድ ልጅ እፍርተዋል::
አቶ ሰለሞን በቤተሰቦቻቸው በዘመዶቻቸው እና በማህበረሰቦቻቸው መካከል የጽድቅ ወንጌልን በቃልና በኑሮ መስክረዋል ለትዳራቸው ታማኝ እግዚአብሄርን የሚፈሩ ቤተሰቦቻቸውን የሚወዱ: ለቤታቸው ካህን: ለባለቤቱ አፍቃሪ ባል ለልጆቹ መልካም አባት ጓደኛ : በአገልግሎታቸው ታማኝ በስራቸው የተወደዱ ትጉህ አና ታታሪ ስው ነበሩ::
እቶ ሰለሞን 11 ወንድሞችና 6 እህቶች የነበሩዋቸው ሲሆኑ ሰፊ ቤተሰብ ውስጥ በማደጋቸው ብዙ የተቸገሩ ሰዎችን ሲያገኙ ወደ ቤታቸው በማስጠጋትና ያላቸውን በማካፈል እራሳቸውን የሚያስችሉ ቅን እና ለጋስ ሰው ነበሩ::
እቶ ሰለሞን አለማየሁ ማክሰኞ ነሃሴ 4 2013 ዓ.ም ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ከቆዩ በኃላ ከዚህ ዓለም ሕይወታቸው አልፏል::
ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን::
A memorial service for Solomon will be held Friday, August 20, 2021 from 1:00 PM to 3:00 PM at Finley Sunset Hills Mortuary, 6801 SW SUNSET HWY, PORTLAND, OR 97225
LIVESTREAM HERE: https://www.facebook.com/FinleySunsetHills
Following the memorial service a graveside service will be held from 3:00 PM to 4:00 PM at Sunset Hills Memorial Park Or, 6801 SW SUNSET HWY, PORTLAND, OR 97225.
Partager l'avis de décèsPARTAGER
v.1.18.0